Tuesday, October 11, 2022

የሚቤዥ አቅም ያለው (ሩት 3:14-18; ሩት 4:1-6)

 ጌታ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ሲናገረ እንዲህ አለ “ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እህቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍ፥ በሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም።” (ማር.10 29፣30፤ እንዲሁም ዕብ.6፡10 ይመልከቱ)፡፡ ሩት በመረጠችው ምርጫ ምንም ቅር አልተሰኘችም፡፡ እንዲሁም ሊከፈላት የሚገባውንም ሽልማት አላጣችውም፡፡ የእግዚአብሔር በረከት በእርሷ ላይ ይሆን ዘንድ ልመናን ያቀረበው ቦዔዝ (2፡12) ራሱ የእምነቷ ካሳ ሆኖ እንደ ሽልማት የተሰጠ ነበር፡፡ይህ ሁኔታ ደግሞ ከጌታና ከሕዝቡ ጋር ካለው ግንኙነት አንጻር እውነታነት አለው፡፡ “ነገር ግን ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቆጥሬዋለሁ፡፡” ብሎ ሐዋርያው ጳውሎስ ይጽፋል፤ ለምን? “ሽልማትን አሸንፍ ዘንድ?” ፈጽሞ አይደለም! “ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ” ይላል (ፊል.3፡8)። 

ነገር ግን አስቀድሞ መተግበር ያለበት አንድ ጉዳይ አለ፡፡ሩት መቤዠት ነበረባት፤ እናም ይህን የእርሷን ከባድ ጥያቄ ለመመለስና መፍትሔ ለማበጀት ቦዔዝ ምንም ጊዜን አላጠፋም፡፡ ምንም እንኳ እርሱ ሊያደርገው የፈለገውን ነገር ቢያውቅም፤ ከእርሱ የቀረበው ዘመድ ግን ሊቤዣት አልቻለም ነበር (ቁ.6)፡፡ መቤዠት ያልቻለው የቅርብ ዘመድ ሰዎችን ሁሉ ማዳንና ወደ እግዚአብሔርም በረከት መምጣት እንዲችሉ ማድረግ ያልቻለውን ሕግ እንድናስብ ያደርገናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በቦዔዝ ውስጥ መለኮታዊ የሆነን ጸጋ እናገኛለን፡፡ ምንም ዓይነት የሚያነሳሳ ነገር ባልተገኘበት በዚያ ወቅት ይህ ጸጋ ቤዛ በሆነው በክርስቶስ ማንነት ውስጥ ተገለጠ፡፡ እርሱ ለእኛ ያለውን ቤዛነት ሁሉ ከፈለ፡፡

No comments:

Post a Comment